Online Admission የቀድሞው ቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የአሁን የለሚኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የተመሰረተበትን 10ኛ ዓመት በማክበር የሥያሜ ለውጡን በይፋ አበሰረ።

የቀድሞው ቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የአሁን የለሚኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የተመሰረተበትን 10ኛ ዓመት በማክበር የሥያሜ ለውጡን በይፋ አበሰረ።

16th September, 2025

ቀን መስከረም 06/2018 ዓ/ም

የቀድሞው ቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የአሁን የለሚኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የተመሰረተበትን 10ኛ ዓመት በማክበር የሥያሜ ለውጡን በይፋ አበሰረ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት እና የእንኳን ደህና መጣቹህ መልክት ያስተላለፉት  የኮሌጁ ዋና ዲን የሆኑት ታደሰ መኮንን(ዶ/ር) ሲሆኑ በመክፈቻ ንግግራቸው  ኮሌጁ ባለፉት 10 አመታት ከ4000 በላይ በደበኛ እና ከ100,000 በላይ የሚሆኑ አጫጭር ሰልጣኞችን በማሰልጠን እና ከ800 በላይ ለሚሆኑ ኢንተርፕራይዞችን  የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ  በማድረግ ለከተማዋ የሰለጠነ የሰው ሀይል  በማፍራት የበኩሉን አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቅሰው  ኮሌጁ በ2018 ዓ/ም በዞንኒንግና ዲፈረንሴሽን በተመረጡ የስልጠና ዘርፎች ሰልጣኞችን ለማሰልጠን ቅድመ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመርሀ-ግብሩ  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምክር ቤት አባልና በቢሮ ሀላፊ ደረጃ የስራና ክህሎት ቢሮ የውጤት ተኮርና ተቋማት ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ  ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ፣በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ  ስር የሚገኙ 14 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲኖች፣ ኢንተርፕራይዞች፣የአካባቢው ማህበረሰቦች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የከተማና የወረዳ አመራሮች  ተገኝተውበታል፡፡
በመርሀ-ግብሩ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ   የውጤት ተኮር ስልጠናና የተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ ኮሌጁ የከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃትና በጥራት እየተወጣ መሆኑንና ከዚህ በላይም መስራት የሚችል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በመድረኩ ኮሌጁ ከተመሰረተ ጀምሮ የኮሌጁን   ታሪካዊ ዳራ የሚያሳይ እና ኮሌጁ ለወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎችን የያዘ ሰነድ በኮሌጁ የሆቴል ቱሪዝም የስልጠና ዘርፍ ተጠሪ በሆኑ በአቶ ዋለ ጌታ ነህ አማካኝነት ቀርቧል፡፡
የኮሌጁ የኢ/ኤ/ቴ/ሽ/ም ዲን የሆኑት ሙሉጌታ አለሙ(ዶ/ር) ኮሌጁ ባለፉት 10 አመታት በርካታ ስራዎችን እንደሰራና ለወደፊትም በርካታ ስራዎችን ለመስራት በእቅዱ የያዘ መሆኑን ገልፀዋል፡፡  
በተጨማሪም ኮሌጁ ከተመሰረተ ጀምሮ የኮሌጁን   ታሪካዊ ዳራ የሚያሳይ  ዶክመንተሪና የፎቶ አውደራዕይ ተካሂዷል፡፡

‹‹የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጁ ኮሙኒኬሽን››

.

Copyright © All rights reserved.

Created with