Online Admission የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት የመሪ እቅድ ውይይት እና ካስኬዲንግ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት የመሪ እቅድ ውይይት እና ካስኬዲንግ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

15th August, 2025

ከፍታን ማፅናት ነገን ማላቅ

የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት የመሪ እቅድ ውይይት እና ካስኬዲንግ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

09/12/2017 ዓ.ም በለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ከፍታን ማፅናት ነገን ማላቅ የ2018 በጀት ዓመት የመሪ እቅድ ውይይት የኮሌጁ አሰልጣኖች እና አስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት ተካሄዷል፡፡
     
       የኮሌጁ ዋና ዲን ታደሰ መኮንን (ዶ/ር) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ኮሌጁ በ 2017 በጀት ዓመት ያስመዘገባቸው ውጤቶች ማስቀጠል ብቻ ሳይሆን ከዛም በተሻለ ማስመዘገብ እንደሚቻል ገልፀው በ2018 በጀት ዓመት የመሪ እቅድ ገለፃ አድርገዋል፡፡ ከቤቱም ለተነሱ ሀሳቦችን እንደ ግብዓት በመውሰድ ለተነሱ ጥያቄዎች በኮሌጁ ዲኖች በጋራ ምላስ ተሰጥቷል፡፡
     
     በመቀጠልም በተደረገው የካስኬዲንግ ፕሮግራም የኮሌጁ ዋና ዲን ታደሰ መኮንን (ዶ/ር) ለስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን ለወ/ሮ ትግስት አይናለም እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ዲን እና  ለተቋም ልማትና አስተዳደር ጉዳዮች ም/ዲን ሙሉጌታ አለሙ (ዶ/ር) የእቅድ ካስኬዲንግ  የፊርማ ፕሮግራም ተከናውኗል፡፡


ለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ

.

Copyright © All rights reserved.

Created with