Online Admission ‹‹በለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ቴክኖሎጅዎችን ለሚሰሩ አሰልጣኞች የቴክኖሎጂ አዋጭነት ትንተና ሰነድ አዘገጃጀት ስልጠና ተሰጠ››

‹‹በለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ቴክኖሎጅዎችን ለሚሰሩ አሰልጣኞች የቴክኖሎጂ አዋጭነት ትንተና ሰነድ አዘገጃጀት ስልጠና ተሰጠ››

31st December, 2025

ቀን ታህሳስ 21/2018 ዓ/ም


‹‹በለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በ2018 ዓ/ም  በጀት ዓመት ቴክኖሎጅዎችን  ለሚሰሩ  አሰልጣኞች የቴክኖሎጂ አዋጭነት ትንተና ሰነድ አዘገጃጀት ስልጠና ተሰጠ››


የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ  ኮሌጅ  የኢ/ኤ/ቴ/ሽ/ የስራ ሂደት በ2018 ዓ/ም  በጀት ዓመት ቴክኖሎጅዎችን  ለሚሰሩ  አሰልጣኞች የቴክኖሎጂ አዋጭነት ትንተና ሰነድ አዘገጃጀት ስልጠና ሰጥቷል፡፡


የኮሌጁ የኢ/ኤ/ቴ/ሽ/ም/ዲን የሆኑት ሙሉጌታ አለሙ (ዶ/ር)  በስልጠናው ላይ በመገኘት የስልጠናው ዋና ዓላማ ወጥና አንድ አይነት የሆነ የቴክኖሎጂ አዋጭነት ትንተና አሰራር እንዲኖር  ለማድረግ እናደሆነ በመግለፅ በ2018 ዓ/ም  የሚሰሩ ቴክኖሎጅዎች ምን ደረጃ ላይ እንደደረሱ ሁሉም አሰልጣኞች የደረሱበትን ደረጃ ገምግመዋል፡፡


ስልጠናውን የሰጡት የቴክኖሎጅ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሀይለእየሱስ ወንዶሰን ሲሆኑ በስልጠናው  አንድ ጥራት ያለውና አዋጭነቱ የተረጋገጠ  የቴክኖሎጅ አዋጭነት ትንተና ሰነድ ለመስራት  መካተት ያለባቸውን መሰረታዊ  ነጥቦች በሰፊው አብራርተዋል፡፡


‹‹የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን››

.

Copyright © All rights reserved.

Created with