Online Admission በ2018 ዓ/ም በኮሌጁ የሚሰሩ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር (Action Research) ፕሮፖዛል ተገመገመ።

በ2018 ዓ/ም በኮሌጁ የሚሰሩ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር (Action Research) ፕሮፖዛል ተገመገመ።

18th December, 2025

ቀን ታህሳስ 09/2018 ዓ/ም 

በ2018 ዓ/ም በኮሌጁ የሚሰሩ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር (Action Research) ፕሮፖዛል ተገመገመ።

የለሚ  ኩራ ማኑፍክቸሪንግ ኮሌጅ በ2018 ዓ/ም የሚሰሩ ችግር ፈቺ  ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (Action Research) ፕሮፖዛል  ከአ/አ የስራና ክህሎት ቢሮ ባለሙያ በመጋበዝ ገምግሟል፡፡

በግምገማው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ የኢ/ኤ/ቴ/ሽ/ም/ዲን የሆኑት ሙሉጌታ አለሙ (ዶ/ር)  የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ዋና ዓላማ  የኮሌጁን ችግር በራስ አቅም በጥናትና ምርምር መፍታት  ሲሆን በኮሌጁ የሚስተዋሉ ችግሮችን  በጥናት ለመፍታት  የስራ ክፍሉ  በበጀት አመቱ  ብዛት ያላቸው የጥናትና ምርምር ርዕሶችን በመለየት እየሰራ ሲሆን በዛሬው ዕለት 8 ፕሮፖዛሎች ተመርጠው ለግምገማ መቅረባቸውን ገልፀዋል፡፡ 

ከቀረቡ 8 የጥናትና ምርምር (Action Research)  ፕሮፖዛሎች ውስጥ  ችግር ፈችነታቸው  ተረጋግጦና ተገምግመው  ለቀጣይ ወደ ተግባር የሚገቡ መሆናቸውንም ተገልፃል፡፡

‹‹የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን››

.

Copyright © All rights reserved.

Created with