Online Admission ‹‹በአዲሱ የሙያ ብቃት ምዘና (COC) አተገባበር ዙሪያ ለሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ››

‹‹በአዲሱ የሙያ ብቃት ምዘና (COC) አተገባበር ዙሪያ ለሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ››

09th February, 2026

ቀን የካቲት 02/2018 ዓ/ም

‹‹በአዲሱ የሙያ ብቃት ምዘና (COC) አተገባበር ዙሪያ ለሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ››


የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም ትምህርታቸውን ላጠናቀቁና በ2018 ዓ.ም ለሚያጠናቅቁ ሰልጣኞች በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ፖሊሲ የሙያ ብቃት ምዘና (COC) አተገባበር ዙሪያ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።


በስልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዋና ዲን ታደሰ መኮንን(ዶ/ር) ይህ ስልጠና የተዘጋጀው በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ እየተተገበረ ባለው አዲስ ፖሊሲ መሠረት ሰልጣኞች ስለ አዲሱ የምዘና ሥርዓት፣ ስለ ዝግጅት ሂደቶች እና ስለ ምዘናው አስፈላጊነት በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው ከወዲሁ እራሳቸውን እንዲያዘጋጁና በምዘናው ብቁ እንዲሆኑ ለማድረግ  ያለመ ስልጠና  መሆኑን ገልፀዋል፡፡ 


የኮሌጁ የስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት አይናለም አዲሱ የቴክኒክና ሙያ ፖሊሲ የሰልጣኞችን ተግባራዊ ክህሎት እና በገበያ ላይ ያላቸውን ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በመግለፅ  የሙያ ብቃት ምዘናው (COC) ሰልጣኞች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ብቁ መሆናቸውን የሚያረጋግጡበት ወሳኝ መሳርያ መሆን ገልፀዋል፡፡


 በስልጠናው በ2017 ዓ.ም ት

ምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ወደ ሥራው ዓለም ከመሰማራታቸው በፊት ይህንን ምዘና ማለፍ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ በ2018 ዓ.ም ለሚያጠናቅቁት ደግሞ ቅድመ-ዝግጅት እንዲያደርና ኮሌጁም ለሰልጣኞቹ አስፈላጊውን ግብዓትና ድጋፍ በማሟላት ለምዘናው ዝግጁ እንዲሆኑና በምዘናው ብቁ እንዲሆኑ  እየሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል።


‹‹የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን››

.

Copyright © All rights reserved.

Created with