Online Admission የወርቃማ ሰኞ የሰራተኞችና የአመራሮች የአብሮነት ጊዜ የእውቀት ሽግግር መርሀ-ግብር ተካሄደ፡፡

የወርቃማ ሰኞ የሰራተኞችና የአመራሮች የአብሮነት ጊዜ የእውቀት ሽግግር መርሀ-ግብር ተካሄደ፡፡

09th February, 2026

ቀን የካቲት 02//2018 ዓ/ም
የወርቃማ ሰኞ የሰራተኞችና የአመራሮች የአብሮነት ጊዜ የእውቀት ሽግግር መርሀ-ግብር ተካሄደ፡፡


የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የሰራተኞች እና የአመራሮች አብሮነት ጊዜ  የእውቀት ሽግግር መርሀ-ግብር አካሂዷል፡፡
ኮሌጁ ዘወትር ሰኞ ማለዳ የሚያካሄደውን የሰራተኞች እና የአመራሮች  የአብሮነት ጊዜ የእውቀት ሽግግር ላይ <<ትውልድን በጋራ መገንባት የወላጆች ተሳትፎ በልጆች ሕይወት ዘርፈ-ብዙ ትምህርት ቤቶች›› በሚል ርዕስ የኮሌጁ የተቋም ልማት ም/ዲን የሆኑት አቶ አብዱልበር መሀመድ ልምድና ተሞክሯቸውን ለሰራተኞች እና ለአመራሮች  አካፍለዋል፡፡


በዕለቱ በነበረው መርሀ ግብር ላይ አቶ አብዱልበር እንደገለጹት፣ ሀገርን የሚረከብ ብቁ ትውልድ ለመፍጠር በተለይም በተወሳሰበና ዘርፈ-ብዙ (Multidisciplinary) በሆነ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ፣ የትምህርት ተቋማት ጥረት ብቻውን በቂ አይደለም።


ይልቁንም ወላጆች በልጆቻቸው ዕለታዊ ሕይወትና ትምህርት ውስጥ የሚያደርጉት ንቁ ተሳትፎ የነገውን ማንነት በመቅረጽ ረገድ ትልቁን ድርሻ እንደሚወስድ አስረድተዋል።
ልጆች  ከሚማሩባቸው ዘርፈ-ብዙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከማሕበራዊ ሚዲያ ፣ከአቻዎች ፣ እንዲሁም ከትምህርት ቤት ውሏቸው ሊማሩ እንደሚችሉ እና የወላጅነት አቀራብ አይነቶች  የፈላጭ-ቆራጭነት (Authoritarian Parenting) ፣የላላ እና ልቅ የሆነ (Permissive Parenting) ፣የገለልተኝነት አቀራረብ (Uninvolved Parenting) እና የተጽዕኖ አሳዳሪነት (Authoritative Parenting) የሚባሉ የወላጅነት አቀራረብ አይነቶች እናዳሉ ም/ዲኑ አክለውም ገልፀዋል፡፡


‹‹የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን››

.

Copyright © All rights reserved.

Created with