Online Admission የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ከሚደረግላቸው ነባር ኢንተርፕራይዞች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ከሚደረግላቸው ነባር ኢንተርፕራይዞች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

21st August, 2025

ነሀሴ 13/2017 ዓ/ም


የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ከሚደረግላቸው ነባር ኢንተርፕራይዞች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡


     የውይይት መድረኩን የመሩት የለሚ ኩራ  ክፍለ ከተማ  ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራ እና ከህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ልመንህ ምህረቱ  ኢንተርፕራይዞች አምራች በመሆናቸው ለሀገር ዕድገትና ብልፅግና ጉዞ ወሣኝ ሚና እንዳላቸው ገልፀው  በዘርፉ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና ብልሹ አሰራሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና ተጨባጭ መፍትሄዎችን በቅንጅት በመፍጠር  ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ  ከሚመለከታቸው አካላት ጋር  የጋራ መግባባት  አስፈላጊ  መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ቤዛ ደመቀ በበኩላቸው  የኢንተርፕራይዞች መነቃቃት ለልማትና እድገት መፋጠን አስተዋጽኦ እንዳለው  ገልፀዋል፡፡


     በውይይት መድረኩ የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ዋና ዲን ታደሰ መኮንን (ዶ/ር) እና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን እና ቴክኖሎጅ ልማት ዘርፍ ም/ዲን ሙሉጌታ አለሙ (ዶ/ር) ኮሌጁ የሚሰጣቸውን ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የኢ/ኤ ድጋፎችን በተመለከተ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን እንደ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ድጋፍ የሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ እንዲሆኑ ከክፍለ ከተማውና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንስራለን ብለዋል።


ለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ
አዲስ አበባ

.

Copyright © All rights reserved.

Created with