Online Admission በመትከል ማንሰራራት! የአረንጓዴ ዓሻራ የችግኝ ተከላ መረሃ-ግብር ተካሄደ፡፡

በመትከል ማንሰራራት! የአረንጓዴ ዓሻራ የችግኝ ተከላ መረሃ-ግብር ተካሄደ፡፡

11th August, 2025

በመትከል ማንሰራራት!

የአረንጓዴ ዓሻራ የችግኝ ተከላ መረሃ-ግብር ተካሄደ፡፡

        በለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ከኮሌጁ አሰልጣኞች፣ አስተዳደር ሰራተኞች፣ ሰልጣኞች እና የለሚኩራ ክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን ከ2500 በላይ ችግኞች ተካላ ተካነውኗል፡፡

    
      የኮሌጁ ዋና ዲን ታደሰ መኮንን (ዶ/ር) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንደ ኮሌጅ መትከል ብቻ ሳይሆን የተተከሉ ችግኞች መንከባከብ እንደሚገባ አሳስባዋል፡፡ 


     በዛሬው ዕለት  ከተተከሉት ችግኞች ውስጥ ለምግብነት የሚውሉ  እንደ አቮካዶ፣ ዘይቱና፣ ማንጎ፣ ወይን እና ሌሎችም  የችግኝ ተክሎች  ተተክለዋል:: 


    የተተከሉት ችግኞች ለፍሬ  ሲበቁ  የአፈርን ለምነት በመጨመር ምርት እና ምርታማነትን የሚጨምሩ፣ የአፈር መሸርሸርን የሚቀንሱ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚረዱ መሆኑ በመርሀ-ግብሩ ተገልፃል::


የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ
05/12/2017 ዓ.ም


.

Copyright © All rights reserved.

Created with