Call us:
+913038373
|
Mail us for help:
bolemanufacturing@aatvetb.edu.et
|
Help center
360° Support - We are here to assist you.
Lemi Kura Manufacturing College
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
Online Admission
Back
Online Admission
Application Form
Registration Form
Status
Announcement
Back
Announcement
News
Notice
Event
Resource
Back
Resource
Publication
Policy&Strategy
Educational Statics
Legal Document
Gallery
Support
Back
Support
Submit Ticket
My Tickets
More
Service
About
Contact Us
Login
Online Admission
በለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ለሴፍትኔት ተጠቃሚዎች የንግድ ክህሎት ስልጠና ተሰጠ
በለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ለሴፍትኔት ተጠቃሚዎች የንግድ ክህሎት ስልጠና ተሰጠ
10th February, 2026
ቀን የካቲት 03/2018 ዓ/ም
በለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ለሴፍትኔት ተጠቃሚዎች የንግድ ክህሎት ስልጠና ተሰጠ
የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት ጋር በመተባበር ለሴፍትኔት ተጠቃሚዎች ለተከታታይ 5 ቀናት የሚቆይ አቅምን የማሳደጊያ የንግድ ክህሎት ስልጠና መስጠት ጀመረ።
የስልጠና ፕሮግራሙን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ ዋና ዲን ታደሰ መኮንን (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ኮሌጁ ከመደበኛ የመማር ማስተማር ስራው ጎን ለጎን ማህበረሰባዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ በመግለፅ ይህ ስልጠና ሰልጣኞች ያላቸውን የተፈጥሮ ክህሎት በሳይንሳዊ የንግድ ስልቶች በመደገፍ፣ ውጤታማ ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ መንገድ የሚጠርግ ስልጠና በመሆኑ ሰልጣኞች በጥብቅ ዲሲፒሊን ስልጠናቸውን እንዲከታተሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የስልጠናው ዓላማ በዋናነት የሴፍትኔት ተጠቃሚዎች የራሳቸውን አነስተኛ የንግድ ስራዎች እንዲጀምሩ፣ የቁጠባ ባህላቸውን እንዲያሳድጉ እና የገቢ ምንጫቸውን በማስፋት እራሳቸውን እንዲችሉ ለማገዝ ያለመ ስልጠና መሆኑ በስልጠናው ተገልፃል፡፡
ሰልጣኞች በአምስቱ ቀናት ቆይታቸው የንግድ ሃሳብ አመራረጥ እና ትግበራ፣የገበያ ትስስር እና የደንበኞች አያያዝ፣የፋይናንስ አስተዳደር እና ቁጠባ እንዲሁም የስራ ፈጠራ ስነ-ልቦና የሚሉ ሀሳቦች ላይ ግንዘቤ እንዲያገኙና ያገኙት እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር ኑሯቸውን ለማሻሻል ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግላቸው ተገልፃል፡፡
‹‹የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን››
.