Online Admission FUGAO

FUGAO

16th September, 2025

ቀን መስከረም 06/2018 ዓ/ም

የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ከFUGAO ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር 1,100 በብር ሲተመን ከ 37 ሚሊዩን ብር በላይ የሚያወጣ መፅሀፍቶችን ለተመረጡ 9ተቋማት በልገሳ መልኩ ድጋፍ አደረገ፡፡
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምክር ቤት አባልና በቢሮ ሀላፊ ደረጃ የስራና ክህሎት ቢሮ የውጤት ተኮርና ተቋማት ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ  ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በዚህ ልክ መደገፋቸው የበቃና የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ሌሎች የቴክኒክና ሙያ ተቋማትም የዚህን አይነት ድጋፍ የሚያገኙበትን መንገድ ቢመቻች ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ዋና ዲን የሆኑት ታደሰ መኮንን(ዶ/ር)  ድርጅቱ ለኮሌጁ ላደረገው ድፍጋፍ የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዬች ም/ዲን የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት አይናለም ከFUGAO ግብረ ሰናይ ድርጅት ለኮሌጁ ድጋፍ የተደረገለትን 150 መፅሀፍቶች በክብር ተረክበዋል፡፡
የኮሌጁ የኢ/ኤ/ቴ/ሽ/ም/ዲን የሆኑት ሙሉጌታ አለሙ(ዶ/ር) ከአጋር ድርጅት ጋር በጋራ መስራት አስፈላጊ መሆኑንና በተደረገውም ድጋፍ ኮሌጁ ተጠቃሚ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የFUGAO ተወካይ የሆኑት ሀብተማሪያም ገ/መስቀል(ዶ/ር) ድርጅቱ ለትርፍ ያልጠቋቋመ መንግስታዊ ተቋም ያልሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅት መሆኑንና በዛሬው ዕለት በስጦታ መልኩ ያደረገው  የመፅሀፍት ድጋፍ FUGAO ግብረ ሰናይ ድርጅት የትምህርት ጥራትን ለማጠበቅ ያለውን ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

‹‹የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጁ ኮሙኒኬሽን››

.

Copyright © All rights reserved.

Created with